“የእድሜ ልክ የሲያትል እና የሰሜን ጫፍ ነዋሪ እንደመሆኔ፣ በማህበረሰባችን ውስጥ ጠለቅ ይለ ታሪክ አሳድሮብኛል። እንደ ቀድሞ የኪንግ ካውንቲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ የቀድሞ የሲያትል የህዝብ ጠበቃ እና የቀድሞ የሲያትል የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሊቀመንበር እንደመሆኔ፣ በሁሉም ማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ሁሉን በመወከል ውጤታማ የሆነ የጥብቅና እና የህዝብ አገልጋይነት ታሪክ አለኝ።

በሲያትል ከተማ ምክር ቤት አውራጃችንን እንድወክል እና በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ሁሉ በክብር፣ በደህንነት፣ እና በጥሩ እድል እንዲኖሩ የሚገፋፋኝ ከከተማችን እና ከዜግነት ተሳትፎ ታሪክ ጋር ያለኝ ግንኙነት ረጅም ነው።

እኔ የእናንተን ድጋፍ በማግኘቴም ክብር ይሰማኛል!”

— Cathy

አውራጃ 5

አውራጃ 5 ከአካባቢዎቿ ከተሞች የሚይካትተው ብዛት ይበልጣል ። የሰሜን ምዕራብ የዩንቨርስቲ የሕክምና ማዕከል ነው ። ሰሜን ሲያትል ኮሌጅ ነው። የአንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም አሉት። መናፈሻዎች, ሐይቆች, ብስክሌት መንገዶች, ማህበረሰብ ማዕከላት, እና ቤተ መጻሕፍት አለው። ኖርዝጌት የገበያ ማዕከል, በበረዶ ጨዋታ/ሆኪ, የፊልም ቲያትር ቤቶች ናቸው። ላይት ሪይል የባቡር ጣቢያዎች፣ ፈጣን የመንዳት አውቶቡሶችና የሦስት አውራ የሆኑ ትልቅ ጎዳናዎች ናቸው። የሁሉም ዓይነት የዓለም አቀፍ ምግቦች፣ የቢራ ጠመቃዎች፣ ቡና ቤቶች እና ማከፋፈያዎች ናቸው። ብዙ ትናንሽ የንግድ ድርጅቶች ናቸው። የሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅቶችና የጋራ እርዳታ ማህበረሰቦች ናቸው። ይህ ቦታ ወጣቶችም ሆኑ አረጋውያን አዲስ የመጡና ለረጅም ጊዜ የሰፈሩበት መኖሪያ ነው። ለዘር፣ ለጎሳና ለማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልዩነት።የስፖርት ሚሊዮን ብር ቤቶች እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አፓርትመንቶች, ነጠላ የቤተሰብ መኖሪያ ቤቶች, ADUs/DADUs/ታውን ሀውስ ቤቶች/አፓርታማዎች. በአጭሩ፣ ተስፋ ሰጪ የወደፊት ተስፋ ያለው ህያውና ባለ ብዙ ገጽታ ያለው አውራጃ ነው።

እንዲሁም በተጨማሪም የአውሮራ ጎዳና ሰሜን ኮሪደር ዳግም ንድፍ የሚያካትት ልዩ ፍላጎቶቻችን ድርሻ አለን፤ በአውሮራ ጎዳና ሰሜን ላይ የወሲብ ዝውውር;  የኖርዝጌት የገበያ ማዕከልእና አካባቢው ቀጣይነት ያለው የድጋሜ እድገት፤ በመጪው ጊዜ የታዘዘ  በ130ኛው የላይት ሪይል ባቡር ጣቢያ ዙሪያ የታዘዘው ጥልቀት፤ ምስራቅ/ምዕራብ ትራንዚት፤ የወደፊቱ የሐይቅ ከተማ ዕቅድ፤ የእግረኛ መንገድ፤ እንዲሁም የቶርተን ክሪክስ የውኃ ማጠራቀሚያ።

በአውራጃ 5 ውስጥ ተገቢውን ተገቢውን የገንዘብ ፍልሰት በመጠቀም እና ውጤታችንን ለማግኘት እና ከተማችን በሚገጥሟት ፈተናዎች ላይ ትርጉም ያለው እድገት ለማድረግ የሚያስፈልገውን ጠንካራ፣ ተሞክሮ ያለው እና የአካባቢ አመራር አመጣለሁ።  ግልጽ እና ተደራሽ እሆናለሁ፣ በፍትሃዊ እና በማህበረሰብ-ተኮር መፍትሄዎች እመራለሁ፣ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ተጠያቂ እሆናለሁ።

 

ስለ እኔ

እናቴ እንደ ብቸኛ ወላጅ ሆና፣ እኔን በሌክ ሲቲ እና በካፒታል ሂል እየተቀምጠን ነው ይሳደገችኝ። እሷም በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ እየሠራች እና በኋላም ለሦስት አስርት ዓመታት የኮሚኒቲ ኮሌጅ ተማሪዎችን በማስተማር ነው እኔን አሳደገችኝ።

እኔም ከህግ ትምህርት ቤት ከወጣሁ በኋላም፣ ለሕዝብ አገልግሎት የእርሷን ፈለግ ተከተልኩ። ለሲያትል ነዋሪዎች ከሲያትል ተከላካዮች ማህበር ጋር የህዝብ ተከላካይ ሆኜ ለብዙዎች ተወክያለሁ፣ እና በኋላም እንደ የቤተሰብ ህግ ጠበቃ ለልጆች እና ቤተሰቦችንም ወክያለሁ። የሲያትል ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሊቀመንበር በመሆን፣ የሲያትል ፖሊስ መሥሪያ ቤት ሕገ መንግሥታዊ ፖሊሶችና ተጠያቂነት እንዲከበር መርቼም ነበር። የአጭር ከተማ ጸሐፊ በመሆኔ የሲያትል ከተማ ምክር ቤት ሕግ አውጪ እንቅስቃሴዎችን በበላይነት እቆጣጠርም ነበር ።

ለእኔ ትልቁ እና ልዩ መብት የተሰጠኝ የሚመስለኝ በኪንግ ካውንቲ የበላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ማገልገል ነበር፣ ያገለገልኩበት፣ ሁሉንም ማህበረሰብም ያለ ምንም ፍርሀት ወይም ውለታ ነበር። በተጨማሪም፣ በወንጀል፣ በቤተሰብ ሕግና በአእምሮ ሕመም ፍርድ ቤት ውሳኔ ከመስጠት፣ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፈርጉሰን በፈርማ ፐርዱ( Pharma Purdue) ላይ የሰጠውን ክስ ደግፌዋለሁ፤ ይህ ክስ ውሎ አድሮ ለኦፒዮድ ሕክምና የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን የሚያስችል ጉልህ እልባት አስገኝቷል። የዘር ፍትህ ለማስፈን ቆርጬ የምሰራው የወንጀል ሕግ ንረት ምጣኔ ሃሳብ ላይ ምስረታ ምጣኔ ሃላፍነት መመውስድ ለውጥ ወይም መሻሻልን አመጣለሁ።

እኔና ባለቤቴ ሦስት ወንዶች ልጆችን አሳደግን፣ አሁን ጎልማሶች እና ሁሉም የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ተመራቂዎች ናቸው። እነዚህ ጊዜያትም ቀላል አልነበሩም። እንደ ብዙዎቹ የሲያትል ሰዎች ሁሉ እኛም በከተማው ውስጥ ቤት ለመግዛት አቅም አልነበርንም፤ በመሆኑም ወደ ሃያ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ተከራይተን ነበር። አንዳንድ ጊዜም ወጪዎቻችንን ለመሸፈን እንታገልም ነበር፤ በተለይ የኢንሹራንስ ኩባንያችን ለባለቤቴ የካንሰር ሕክምና ሽፋን ከለከለ እና ከስራው ካሰናበቱት በኋላ።   ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሶስቱም ወጣት ልጆቼ በጉርምስና ዕድሜ ቤት ውስጥ እያሉ በአሰቃቂ ሁኔታ በድንገት እናቴ አስከፊ የሆነ ስትሮክ ይዛት በዚህም ምክንያት ለእናቴ እንክብካቤ ማድረግ ጀመርኩ።

ዛሬ ባለቤቴ የተሳካ አነስተኛ፣ ስኬታማ ንግድ አለው እና ይሰራል፣ እኛ የቤት ባለቤቶች ነን፣ ሁላችንም ጤነኞች ነን፣ እና ልጆቻችን የየራሳቸውን ኑሮ በዚች አለም ላይ መንገዳቸውን ጀምረዋል። እኔና ቤተሰቤም እኛ ያገኘናቸውን መብቶችና መልካም ነገሮች ለማግኘት፣ ለሁሉም የሲያትል ነዋሪዎች እና ተወላጆች ይህንን እንዲያገኙ ለመኖር የሚቻልበት ከተማ መፍጠር የእኔ ተልእኮ ነው።