ለጤናማ እና ለበለጸገ ሲያትል ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች
የችግር መንስኤዎችን ማወቅ እና ውጤቶችን ማግኝት
እንደ ዳኛ እና ጠበቃ፣ እኔ ሁሌም ተጠያቂነትን እና ፍትህን እንዴት እንደምናገኝ እንዲሁም በሱስ መጎዳትን እና ህገ-ወጥ ባህሪን በማቆም ላይ ሁልጊዜ አተኩሬያለሁ። ለሕዝብ ደህንነት ሲባል ይህንን ሁለገብ ባለብዙ ገፅታ ትኩረት እንዲሰጠው ወደ ምክር ቤት አቀርባለሁ፣ ለጥሪም ምላሽ በፍጥነት ለማግኘት ወይም ጊዜን ለማሻሻል ተጨማሪ በከፍተኛ ሁኔታ የሰለጠኑ ፖሊሶችን መቅጠር፣ በደንብ ከሚታመን ምንጭ የተገኘ መረጃ እንዲሁም ተጨማሪ አማራቾን የኖዋሪዎች ምላሽ ለማኘት መርሃ ግብር መፍጠር፣ እንዲሁም ስኬታማ እና ጤናማ የሆኑ የከተማ ፍርድ ቤት ፕሮግራሞችን መቀጠል።
በተጨማሪም፣ በከተማችን ውስጥ ለረጅም ጊዜ የጠፋውን እና የሰው ህይወት ያጠፋውን የጠመንጃ ጥቃት ማስቆም አለብን። እንደ ዳኛ ከአሁን በፊት እጅግ በጣም አደገኛ ጥበቃ ትዕዛዞችን በመስጠት ከተለዋዋጭ ወይም ከተጨነቁ ግለሰቦች ሽጉጥ ተወስዶባቸዋል፣ የእነዚህን ትዕዛዞች ኃይልም ሕይወትን ለመጠበቅ እንደሆነም ይገባኛል። በከተማው ውስጥ ከፍተኛ የአደጋ መከላከያ ትእዛዞችን መጠቀምን ለማስፋፋት እሰራለሁ። በተጨማሪም፣ የሲያትል ነዋሪዎችን የመጠበቅ ችሎታ የሚያደናቅፉ ጉዳዮችን የአካባቢ ጥበቃ ህጎችን ለማንሳት በመንግሥት ደረጃ እሰራለሁ።
በአስቸካይም፣ በከተማው ውስጥ ብጥብጥ እና አመጽ እንዳይቀጥል መርሃግብርን በመመስረት ለማሻሻል እና ለማስፋፋት እሰራለሁ፣ እንዲሁም፣ የድረ ገጽ ሓሳብ እና አስተያየቶችን በመስማት ማህበራዊ ወሳኔ የጠመንጃ ጥቃት ገንዘብን ስራ ላይ በማዋል፣ ለማስተማር፣ የስራ ስልጠና እና ክህሎት፣ ምክር መስጠትና ማኅበራዊ ግንኙነቶች መጨመር።
የባህርይ ጤና ከቀረጥ የተገኘ ገንዘብ ውጤት ምንም ይሁን ምን በሲያትል ውስጥ ለሚገኘው የአእምሮ ጤና ቀውስ እንክብካቤ ማእከል ጥብቅና አደርጋለሁ። በተጨማሪም፣ ለሜታምፌታሚን፣ ለአልኮል መጠጥ አጠቃቀምና ለኦፒዮድ አጠቃቀም የሚያስፈልገውን መድኃኒት ለመፍጠር የሚደረገውን ማንኛውንም ጥረት እደግፋለሁ።
ተመጣጣኝ እና የአካባቢን ገንዘብ ለስራ መመደብ
እኔ እንደ እናት መሆኔ፣ ወንድ ልጆቼ ለእነሱ ትርጉም ያለው ስራ እንዲሰሩ እና አሁንም በሲያትል የመኖር አቅም እንዲኖራቸው እፈልጋለሁ። አሁን ባለው የመኖሪያ ቤት አቅም ችግር፣ ይህ ለእነርሱ ወይም ለብዙ ሰራተኞች፣ ቤተሰቦች እና ወጣቶች በተለይም በቢአይፒኦክ ማህበረሰቦች ውስጥ የማይቻል ነው።
አሁን የከተማችንን ቅርፅ ለመጪዎቹ አመታት ለመንደፍ በሲያትል አጠቃላይ ፕላን ክለሳ በኩል ለማስተካከል በቀጣይ እቅድ ለማውጣት እድል አለን። እንድ አማራጭ 2, 3, 4, እና 5 (አማራጭ 1 ምንም አለማድረግ ነው) በእቅዱ ውስጥ ሁሉም በርካሽ የመኖሪያ ቤት መጨመር አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን ያካትታል። አውራጃ 5፣ ነገር ግን፣ የመኖሪያ ቤት መፈናቀል ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠባቸው አካባቢዎችም ይጠቃቅላል፣ እነኝህም ከተሞች ሌክ ሲቲ፣ ቢተር ሌክ እና ኖርዝጌትን ይጨምራል። እኔ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት በእነኝህ ከተሞች ውስጥ የከተማ አቀፍ ደረጃ ተመጣጣኝ ቤቶችን በተሳካ ሁኔታ የሚጨምር አማራጭን ለመደገፍ እሞክራለሁ።
በምክር ቤቱ ላይ ም/ቤት ላይ ደግሞ አውራጃ 5 ውጤታማ እና አስተማማኝ የአውቶቡስ አገልግሎት, ብስክሌት እና የእግረኞች ደህንነት, የተጠቀለሉ አገልግሎቶች, የወጣቶች ተሳትፎ, እና ሌሎች ምስረታዎችን ጨምሮ የአውራጃውን እያደገ ያለውን ፍላጎት ለማሟላት ተገቢውን የመሰረተ ልማት መዋዕለ ንዋይ እያገኘ መሆኑን አረጋግጣለሁ.
እኩል ዕድል ለሁሉም
የእኛ ሰፈሮች የሚገለጹት በምንወዳቸው የአካባቢ ንግዶች፣ ከፍ አድርገን በምንመለከታቸው የአካባቢው ድርጅቶች ተለይተው ይገለጻሉ፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የአካባቢው አስተዳደር ህግ እና ደንብ እየተመሩ ድምፃቸው እና ስጋታቸው ጠፍቷል፣ የከተማ መመሪያዎችን እና አጀንዳ በማውጣትን እንፈታዋለን። በከተማችን ውስጥ የበለጸገ፣ የሚቋቋም ኢኮኖሚ ለመገንባት የአካባቢው ንግድ ቤቶችና ሬስቶራንቶች፣ የመደብር ፊት ቸርቻሪዎች፣ ሴቶች እና የ BIPOC ባለቤት የሆኑ የንግድ ድርጅቶች እና ሌሎች የአገር ውስጥ ሥራ ፈጣሪዎች በከተማው ከንቲባ መወከላቸውን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ።
የሶስት ጎልማሶች እናት እንደመሆኔ፣ ሁሉም የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተመራቂዎች እንደመሆናችው፣ እያንዳንዱ ልጅ የቤተሰብ ደሞዝ ሥራ የማግኘት መንገድ እንዲኖረው በከተማ፣ በትምህርት የአውራጃ፣ በንግድ እና ቴክኒካል ትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን አጋርነት ለማሳደግ በጥልቅ ለመስራት ቆርጬያለሁ።